አማርኛ English
ለበለጠ መረጃ

የአፈ ጉባኤ መልዕክት

የአፈ ጉባኤ ፎቶ

የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ሐጀዙሊ

የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

እንደሚታወቀው የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት በተሻሻለው የከተማ አስተዳደሩ ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 መሰረት ግንቦት12/2000 ዓ/ም ከቻርተሩ የመነጩ ህግ የማውጣትና አስፈፃሚ አካላትን የመከታተልና የመቆጣጠር ስልጣን ይዞ ከሶስቱ የመንግስት አካላት አንዱ ህግ አወጭ አካል ሆኖ ተመስርቷል፡፡

እንደተመሰረተ ባለፉት ሁለት የምርጫ ወቅቶች የገጠሙትን ልዩ ልዩ ተግዳሮቶች አልፎ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ከዓመት ዓመት ራሱን በአሰራር፣ በአደረጃጀትና በግብዓት እያደራጀ እና እያሻሻለ በመምጣቱ አሁን ላይ ውጤታማ ስራ በማስመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡

ሙሉ መልዕክቱን ያንቡ

አመሰራረት

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ታሪክ እና አደረጃጀት

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ታሪክ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት በ1879 ዓ.ም የተቆረቆረች ሲሆን 139 ዓመት ዕድሜዋ ላይ ትገኛለች፡፡ ከተማዋ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ የአስተዳደር ዘይቤዎችንና ስርዓቶችን ስታስተናግድ የቆየች ሲሆን በነዋሪዎቿ የነቃ ተሳትፎ ለከተማዋ እድገትና ለሀገር ግንባታ የበኩሏን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አስተዋፅኦ ያበረከተችና አሁንም በማበርከት ላይ የምትገኝ ናት፡፡

የምክር ቤቱ ዋና ሚና

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማው ህግ አውጪ ተቋም ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ ላይ የሚደረጉ ውሳኔዎችን በማሻሻልና በማረጋገጥ ረገድ ዋና ሚና ይጫወታል።

መጀመሪያ ምክር ቤት (2000 ዓ.ም)

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህገ መንግሥት አንቀጽ 49፣ በአዋጅ ቁጥር 361/1995 ተሻሽሎ በወጣው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማቋቋሚያ ቻርተር መሠረት ግንቦት 12 ቀን 2000 ዓ.ም ትክክለኛውን የምክር ቤት ቅርፅ የያዘ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ተመሰረተ፡፡

ምክር ቤቱ እንደ ህዝብ እንደራሴነት ራሱን ችሎ ሲቋቋም የመጀመሪያው ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ማለትም ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ከተማ አቀፍ ህጐችን በማውጣት ለከተማዋ ነዋሪ ተደራሽ ከማድረግ ጐን ለጐን በከተማው የሚገኙ አስፈፃሚ አካላት ከተቋቋሙበት ዓላማና ተልዕኮ አንፃር ለህብረተሰቡ የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል እየተከታተለ ድጋፎችንም ሲሰጥ የቆየና አሁንም የዘወትር ተግባሩን ያለመታተር በማከናወን ላይ የሚገኝ የህዝብ ምክር ቤት ነው፡፡