የመንግስት ዋና ተጠሪ ተግባር እና ኃላፊነት
የመንግስት ዋና ተጠሪ
በአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ተግባር እና ኃላፊነት፣ አደረጃጀት እና አሰራር በም/ቤት አሰራርና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ ቁጥር 12/2016 ክፍል አስራ ሶስት ከአንቀፅ 108 እስከ 110 በግልፅ ተዘርዝሮ ተቀምጧል፡፡
የመንገስት ተጠሪ ተግባርና ኃላፊነት በሁለት የሚከፈል ሲሆን:
1. በም/ቤቱ የመንግስት ስራን ከመንግስት ተጠሪ አኳያ የማስተባበርና የመምራት።
2. በም/ቤቱ የገዥውን ፓርቲ ወክሎ የፓርቲ አደረጃጀትን የሚያስተባበርና የሚመራ። በሁለቱም ተግባርና ኃላፊነቶች የመንግስት እና የፓርቲ ተጠሪዎችን አሰያየም፣ ተጠሪነትና ተግባርን የሚያጠቃልል ነው፡፡
አንቀፅ 108: የመንግስት ተጠሪዎች አሰያየምና ተጠሪነት
- 1. አንድ ዋና ተጠሪ እና ከሶስት የማይበልጡ ረዳት ተጠሪዎች በከተማ ከንቲባ የሚሰየሙ ሲሆን ረዳቶቹ ከንቲባና ዋና ተጠሪ ጋር በመመካከር ይሰይማቸዋል።
- 2. የመንግስት ዋና ተጠሪ ተጠሪነቱ ለከንቲባ ነው።
- 3. የመንግስት ረዳት ተጠሪ ተጠሪነቱ ለዋናው ተጠሪ ነው።
አንቀፅ 109: የመንግስት ተጠሪዎች ተግባርና ኃላፊነት
- 1. የምክር ቤት ሥራዎችን እና አሠራሮችን በመንግስት አቅጣጫ መምራት፣ ተግባራዊ ማድረግ።
- 2. የሚቀርቡ የአስተዳደር አጀንዳዎችን ለአፈ ጉባኤ አቅርቦ ማስወሰን።
- 3. ከአስፈፃሚ ተቋማት ጋር ግንኙነት መፍጠርና ስራን ማከናወን።
- 4. የዋና ተጠሪ መኖሩ ቢቋረጥ፣ ከረዳቶቹ መካከል የሚወክል መምረጥ።
- 5. ተለይተው የሚሰጡትን ተግባራት የሚያከናውኑ ነው።