የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የአፈ ጉባኤ ልዩ ጽ/ቤት
ክቡር አቶ መንግስቱ ላማሮ
የአፈ ጉባኤ ልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ

የአፈ ጉባኤ ልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት

የአፈ ጉባኤ ልዩ ጽ/ቤት

1. ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለአፈ ጉባኤ የሆኑ የምከር ቤት አካላት (እማካሪ ኮሚቴ፣ አስተባባሪ ኮሚቴ፣ ተጠሪ ተቋማት ፣የክፍለ ከተማ ምክር ቤቶች እና አማካሪዎች) እና ስራዎቻቸውን ያስተባብራል፣ ያቀናጃል፤ የውሳኔዎቻቸው መረጃ ተደራጅቶ እንዲቀመጥ ያደርጋል፣ አፈጻጸማቸውን ተከታትሎ ሪፖርት ለአፈጉባኤ ያቀርባ፤

2. የምክር ቤቱ አመራሮችና እንግዶች እንዲሁም ሁነቶች ፕሮቶኮላቸው እንዲጠበቅ ፣ሁነቶች የምክር ቤቱን ክብርና ደረጃ በጠበቀ መልኩ እንዲፈጸሙ ተከታትሎ ይደግፋል፣ መስተንግዶዎች ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲፈጸሙ ያመቻቻል ፤ያስተባብራል፣

3. ለአፈ ጉባኤና ለእንግዶቻቸው የሚቀርቡ አገልግሎቶችን ፍላጎቶችና ጥያቄዎች ከአፈጉባኤው እና ከሚያስተባብራቸው ሌሎች አካላት በመሰብሰብ አገልግሎቶ እንዲቀርቡ ያደርጋል፤ ያመቻቻል፤ ተፈጻሚነታቸውን በመከታተል ችግር ሲያጋጥም ፈጥኖ መፍትሄ ይሰጣል/ያስጣል

4. የሚያስተባብራቸው የሥራ ክፍሎች እቅድ በተቀመጠለት ጊዜና በጀት መሠረት እየተፈጸመመ ሆኑን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ሪፖርት በመቀበልና ውሳኔ እንዲሰጥበት ያደርጋል፤

5. ከእንግዶች ጋር የሚያዙ ቀጠሮዎች እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ያመቻቻል ! ተከታትሎ እንዲፈጸሙ ያደርጋል፡


6. በአፈ ጉባኤ የሚመሩ ሁነቶች፤ ጉባኤ እና ስብሰባዎች መርሐ-ግብር ያወጣል!፤ተፈጻሚነታቸውን ይከታተላል ፤

7. ለሁነቶችና መድረኮች አስፈላጊ ግብዓቶች (የመድረኮቹን ባህሪይ በማጥናት የሚተላለፉ መልዕክቶች እና አቀራረብን ጨምሮ) አጠቃላይ ሁኔታዎች እንዲሟላ ያደርጋል፤

8. በቀጥታ ከአፈ ጉባኤ ጋር የሚደረጉ የሚዲያ ግንኙነት እና የፕሬስ ስራዎች ያቀናጃል። በማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚደረጉ የተግባቦት ስራዎችን ይከታተላል፣ ያስተዳድራል፤

9. የሚያስተባብራቸው አካላት ስራዎች ዕቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት ተደራጅቶ እንዲቀርብ ያደርልጋል፤ የአፈጻጸም ምዘና ሃደት ያመቻቻል፤ መረጃዎችን አደራጅቶ ይይዛል፤

10. ሙያዊ ደጋፊ ለሌላቸው የምክር ቤት አካላት እንደ እስፈላጊነቱና እንደ ወቅቱ ባለሙያ (ፎካልፐርሰን) እንዲመደብና ስራዎቹ እንዲፈጸሙ ያስተባብራል፣

11. ወቅታዊና ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ተቋማዊ ሆነው እንዲመሩ ከእማካሪዎች እና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ጋር በትብብር ይሰራል፣ ያስተባብራል፤

12. በልዩ ሁኔታ በአፈ ጉባኤ የሚሰጡ ተጨማሪ ስራዎችን ያከናውናል፤