ተቋማዊ አገልግሎቶች

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለከተማው ህዝብ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በተሻለ ጥራት እና በፍጥነት ለማድረስ ቁርጠኛ ነው።

የምክር ቤቱ አጠቃላይ እይታ

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የከተማው ህዝብ የሉዓላዊነት መገለጫና የከተማው ከፍተኛ የሥልጣን አካል ነው፡፡ ም/ቤቱ በቻርተሩ በተሰጠው የሥልጣን ከተማ አቀፍ ህጎችን ያወጣል፤ የወጡትንም ህጎች ተግባራዊነት ይቆጣጠራል፣ይከታተላል፡፡

የአስፈጻሚ አካላትን ዕቅድና አፈፃፀም በመገምገም፣ በመከታተልና በመቆጣጠር ለከተማዉ ነዋሪዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ተግባራዊ መሆናቸዉን በማረጋገጥና የም/ቤቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ለከተማው ነዋሪ ተደራሽ በማድረግ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የበኩሉን ሁሉ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ ህግ በማውጣት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ሂደትም የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ጽ/ቤት አስተዳደራዊ ድጋፍ የመስጠት ተግባሩን ያከናውናል፤ በመሆኑም ምክር ቤቱ ከተማዋ ለጀመረቻቸው ለዉጥ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታዎች፣ ለፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት እንዲሁም ለመልካም አስተዳደር መስፈን የሚረዱ ተጨባጭ ሁኔታ ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚጣጣሙ ህጎችን በማውጣት ስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል።

  • ህግ ማውጣት እና ማሻሻል
  • የአስፈጻሚ አካላት ክትትልና ቁጥጥር
  • የህዝብ ተሳትፎ ማስፈን
  • የበጀት ማፅደቅ እና ክትትል
  • የልማት ፕሮጀክቶች መከታተል
  • የህዝብ ቅሬታዎችን መፍታት
90+
የወጡ ህጎች
6
ቋሚ ኮሚቴዎች
130+
የምክር ቤት አባላት
95%
የህዝብ እርካታ

ዋና ዋና አገልግሎቶች

ምክር ቤቱ ለህብረተሰቡ የሚያቀርባቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች

ህግ ማውጣትና ማሻሻል

የከተማ አቀፍ ህጎችን ማውጣት፣ ማሻሻል እና መተርጎም በማድረግ ለከተማው ህዝብ ፍትሃዊ አገልግሎት ለማበርከት ይሰራል።

  • አዳዲስ ህጎችን ማዘጋጀት
  • ያሉ ህጎችን መከለስ
  • የህዝብ አስተያየት መሰብሰብ
ተጨማሪ ያንብቡ

ክትትልና ቁጥጥር

የአስፈጻሚ አካላት እንቅስቃሴ መከታተል እና መቆጣጠር በማድረግ አገልግሎቶች በተገቢው መንገድ መሰጠታቸውን ያረጋግጣል።

  • የበጀት አፈፃፀም ክትትል
  • የፕሮጀክቶች ቁጥጥር
  • የአፈፃፀም ግምገማ
ተጨማሪ ያንብቡ

የህዝብ ተሳትፎ

የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማስፈን እና ማጎልበት በማድረግ ህዝብ በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ እንዲሳተፍ ያደርጋል።

  • የህዝብ መድረኮች
  • የአስተያየት መስጫ መድረኮች
  • የማህበረሰብ ተሳትፎ ፕሮግራሞች
ተጨማሪ ያንብቡ

የበጀት አስተዳደር

የከተማውን በጀት ማፅደቅ፣ መከታተል እና ቁጥጥር ማድረግ የምክር ቤቱ ዋና ተግባር ነው።

  • ዓመታዊ በጀት ማፅደቅ
  • የበጀት አፈፃፀም ክትትል
  • የሂሳብ ኦዲት
ተጨማሪ ያንብቡ

የልማት ፕሮጀክቶች

የከተማ ልማት ፕሮጀክቶችን መከታተል እና መገምገም የምክር ቤቱ ኃላፊነት ነው።

  • የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች
  • የማህበራዊ አገልግሎት ፕሮጀክቶች
  • የኢኮኖሚ ልማት ፕሮጀክቶች
ተጨማሪ ያንብቡ

የህዝብ አገልግሎት

የህዝብ ቅሬታዎችን መቀበል እና መፍታት የምክር ቤቱ ዋና ተግባር ነው።

  • ቅሬታዎችን መቀበል
  • አስተያየቶችን መሰብሰብ
  • መረጃ መስጠት
ተጨማሪ ያንብቡ

6 ቋሚ ኮሚቴዎች

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች እና የሚከታተሏቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች

ፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮችን የሚከታተል እንዲሁም በዘርፉ ያሉ ፖሊሲዎችን በመገምገም ለምክር ቤት የሚያቀርብ ኮሚቴ።

+251 114 70 45 33
justice@aacitycouncil.gov.et
የኮሚቴው ሰብሳቢ እና ኃላፊነት

ፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፍትህ ስርዓትን፣ መልካም አስተዳደርን እና ህግ የበላይነትን የማስፈን ኃላፊነት ተጥሎበታል።

የሚከታተላቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች፦
  • የከንቲባ ጽ/ቤት
  • የፍትህ ቢሮ
  • የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮና ተጠር ተቋማት
  • ሀ/ የደንብ ማስከበር አገልግሎት ባለስልጣን
  • የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ
  • ኮሚኒኬሽን ቢሮ
  • አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ
  • የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን
  • ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን
  • የከተማ ቦታ ማስለቀቅ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ
  • የመሬት ይዞታ ማስለቀቅ እና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤ
  • የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች (ይግባኝ ሰሚና የመጀመሪያ ፍርድ ቤት)
  • የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች

የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን እና ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎቶችን የሚከታተል ኮሚቴ።

+251 114 70 45 33
infrastructure@aacitycouncil.gov.et
የሚከታተላቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች፦
  • ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ተጠሪ የሆኑ ተቋማት
  • የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
  • የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ
  • የሲቪል ምዛገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
  • ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን
  • መንገዶች ባለስልጣን
  • የኤሌትሪክ ሀይል አገልግሎት/የአዲስ አበባ ዲስትሪክት/
  • የትራንስፖርት ቢሮ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት
  • የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን
  • የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን
  • የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
  • የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት

የሴቶች፣ ህፃናት፣ ውጤቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚከታተል ኮሚቴ።

+251 114 70 45 33
women@aacitycouncil.gov.et
የሚከታተላቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች፦
  • የሴቶች፣ ህፃናት፣ ውጤቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
  • ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
  • ትምህርት ቢሮ
  • ጤና ቢሮ
  • የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን
  • የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን
  • ትምህርት፣ ስልጠናና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን
  • የምገባ ኤጀንሲ
  • የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ
  • ማህበራዊ ትሬስት ፈንድ

የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ቱሪዝም ዘርፎችን በመከታተል እና በመቆጣጠር የዘርፉን ልማት የሚያረጋግጥ ኮሚቴ።

+251 114 70 45 33
trade@aacitycouncil.gov.et
የኮሚቴው ሰብሳቢ እና ኃላፊነት

የንግድ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ልማት የማስፋፋት ኃላፊነት ተጥሎበታል።

የሚከታተላቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች፦
  • የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
  • ንግድ ቢሮ
  • የሥራና ክህሎት ቢሮ
  • የባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ
  • ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
  • የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ
  • ህብረት ስራ ኮሚሽን
  • አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን
  • የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ

የመንግስት በጀት አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የመንግስት በጀት አስተዳደርን፣ አፈፃፀምን እና ቁጥጥርን የሚከታተል ኮሚቴ።

+251 114 70 45 33
budget@aacitycouncil.gov.et
የኮሚቴው ሰብሳቢ እና ኃላፊነት

የመንግስት በጀት አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የበጀት ዲሲፕሊን እና የፋይናንስ አስተዳደርን የማስፈን ኃላፊነት ተጥሎበታል።

የሚከታተላቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች፦
  • ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት
  • የገቢዎች ቢሮ
  • የፋይናንስ ቢሮና ተጠር ተቋም
  • ሀ/ የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
  • የመንግስት ልማት ድርጅቶች አገልግሎት
  • የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን

የመሬትና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የመሬት አስተዳደር፣ የግንባታ ፕሮጀክቶች እና የከተማ ልማት ጉዳዮችን የሚከታተል ኮሚቴ።

+251 114 70 45 33
land@aacitycouncil.gov.et
የኮሚቴው ሰብሳቢ እና ኃላፊነት

የመሬትና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመሬት አጠቃቀምን፣ የግንባታ ደረጃዎችን እና የከተማ ልማትን የማስተካከል ኃላፊነት ተጥሎበታል።

የሚከታተላቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች፦
  • የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
  • የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ
  • የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮና ተጠር ተቋም
  • ሀ/ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
  • የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
  • የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን
  • የፕላንና ልማት ቢሮ
  • የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ተጠር ተቋም
  • ሀ/ የጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል
  • የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

የምክር ቤት ስብሰባዎች መቼ ነው የሚካሄዱት?

የምክር ቤት መደበኛ ስብሰባዎች በየሁለት ሳምንቱ ማክሰኞ እና ረቡዕ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 5:30 ይካሄዳሉ። ልዩ ስብሰባዎች እንደአስፈላጊነቱ ይጠራሉ። ስብሰባዎች ለሕዝብ ክፍት ናቸው እና በምክር ቤቱ ግቢ ውስጥ ይካሄዳሉ።

የህዝብ ቅሬታዎችን እንዴት ማቅረብ ይቻላል?

ቅሬታዎችን በአራት ዋና መንገዶች ማቅረብ ይቻላል፡-
1. በአካል በመቅረብ (ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 እስከ 11፡30)
2. በስልክ፡ +251 114 70 45 33
3. በኢሜይል፡ info@aacitycouncil.gov.et
4. በድህረ ገጻችን በአስተያየት መስጫ በኩል

የምክር ቤት አባላትን እንዴት ማግኘት ይቻላል?

የምክር ቤት አባላትን በስራ ሰዓት በምክር ቤት ግቢ፣ በስልክ ወይም በኢሜይል ማግኘት ይቻላል። የእያንዳንዱ አባል የመገኛ አድራሻ እና የእውቂያ መረጃ በድህረ ገጻችን ላይ በ"የምክር ቤት አባላት" ክፍል ውስጥ ተዘርዝሯል።

ማንኛውም አስተያየት ወይም ጥያቄ አለዎት?

ያለዎትን ማንኛውም ሀሳብ፣ ቅሬታ ወይም ጥቆማ በአስተያየት መስጫ ላይ ያስፍሩ። ስለሚሠጡን ሀሳብ ከወዲሁ እናመሠግናለን።