የንግድ፣ ኢንደስትሪ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቂርቆስ እና አዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሚገኙ የዘርፍ ኮሚቴዎችን የ9 ወራት የስራ እንቅስቃሴ ገምግሟል

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 89


የንግድ፣ ኢንደስትሪ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቂርቆስ እና አዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሚገኙ የዘርፍ  ኮሚቴዎችን የ9 ወራት የስራ እንቅስቃሴ ገምግሟል

የንግድ፣ ኢንደስትሪ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቂርቆስ እና አዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሚገኙ የዘርፍ ኮሚቴዎችን የ9 ወራት የስራ እንቅስቃሴ ገምግሟል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር አቶሜ አበበ እንደገለጹት ሱፐርቪዥኑ የክ/ከተማ የዘርፍ ኮሚቴዎችን የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ለመገምገም ብሎም የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ ለማድረግና አሠራሮችን ለመመልከት ብቻ ሳይሆን በቼክ ሊስቱ መሠረት አፈጻጸሞችን በመገምገምና ያሉበትን ሁኔታ በመለየት ለቀጣይ ስራዎች ስኬት አቅጣጫ ማስቀመጥ መሆኑን ገልጸዋል።
በመቀጠል በቂርቆስ ክ/ከተማ የንግድ፣ ኢንደስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጀኢላን አብዲ በኮሚቴው ባለፉት 9 ወራት በዘርፉ የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።
ቋሚ ኮሚቴውም በቼክ ሊስቱ መሰረት በክ/ከተማው የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ የተዘጋጁ የተለያዩ ሰነዶችን ለመመልከት ችሏል።
ቋሚ ኮሚቴው በመድረኩ መጨረሻ የቃል ግብረ መልስ የሰጠ ሲሆን በዚህም በጥንካሬ ተናባቢ እቅድ መዘጋጀቱ፣ ጠንካራ የሆነ የሰነድ አያያዝ መኖሩ እንዲሁም ወጥ የሆነ የግብረ መልስ አሰጣጥ ስርዓት መኖሩን ገልጸው፤ ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ፣ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ላይ እየተሰሩ ያሉ የሪፎርም ስራዎችን ከመከታተልና ከመደገፍ አኳያ እና ከልማት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ኢንተርፕራይዞች ተለዋጭ ቦታ እንዲሰጣቸው ከማድረግ አኳያ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ መሆን አንዳለበት አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ቋሚ ኮሚቴው የከሰዓት በኋላ ምልከታውን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ንግድ፣ ኢንደስትሪ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ዘርፍ ኮሚቴ ላይ ያደረገ ሲሆን የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢቲሳ ደሜ ሱፐርቪዥኑ በዋናነት የልምድ ልውውጥ ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸው፤ አክለውም ባለፉት 9 ወራት የተሰሩ ስራዎችን እንደሚመለከት አመላክተዋል።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ም/ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ በቀለ ጉታ በበኩላቸው ሱፐርቪዥኑ ያለውን ጠቀሜታ ገልጸው፤ በዘርፉ የቅሬታ አቀራረብ ስርዓት ስለመኖሩ፣ከክትትልና ቁጥጥር አኳያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ እንዲሁም የልምድ ልውውጥና ተሞክሮዎችን ከተለያዩ አቻ ተቋማት ጋር መወሰዱን ጨምሮ ሰፋ ያለ ማብራርያ ሰጥተዋል።
በክ/ከተማው የዘርፉ ባለሙያም የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም የቀረበ ሲሆን፤ቋሚ ኮሚቴውም በቼክ ሊስቱ መሰረት በክ/ከተማው የዘርፉ ቋሚ ኮሚቴ ባለፉት 9 ወራት የተዘጋጁ ሰነዶችን ተመልክቷል።
በመጨረሻም ቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ኢቲሳ ደሜ የቃል ግብረ መልስ የሰጡ ሲሆን በዚህም በጥንካሬ በርካታ ጠንካራ ጎኖች መኖራቸውን ገልጸው፤ በቀጣይ ከስራ እድል ፈጠራ አኳያ እና የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ላይ የክ/ከተማው የዘርፍ ኮሚቴ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በአብርሃም አበበ
መጋቢት 24/2016 ዓ.ም



Leave a Comment: