የንግድ ፣ኢንደስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከጉለሌ ክ/ከተማ የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ።
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 78
በአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የንግድ፣ኢንደስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጉለሌ ክ/ከተማ የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ።
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ኢቲሳ ደሜ እንደገለጹት ምልከታው በዋናነት አሰራሮችና ተሞክሮዎች ላይ ልምድ ለመለዋወጥ መሆኑን ገልፀው፤ በተዘጋጀው ቼክ ሊስት መሰረት በጉለሌ ክ/ከተማ የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ የግብረመልስ አሰጣጥን፣ የቅሬታ አፈታት ስርዓትን በተመለከተ እንዲሁም ከአቅም ግንባታ ስራዎችን ጨምሮ የተሰሩ ስራዎች ላይ ምልከታው እንደሚያተኩር ጠቁመዋዋል።
የጉለሌ ክ/ከተማ ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መኩሪያ ጉርሙ በበኩላቸው ም/ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህ የልምድ ልውውጥ ተሞክሮዎችን ከመለዋወጥ አንጻር እና የቋሚ ኮሚቴዎችን የመከታተልና የመቆጣጠር አቅም ከማሳደግ አንጻር እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር አቶሜ አበበ በሰጡት ማጠቃለያ መድረኩ ጥንካሬና ክፍተቶችን መማማርያ መሆኑንና ፤በርካታ ውጤታማ ስራዎች መሠራታቸውን የገለጹ ሲሆን በቀጣይም ከስራ እድል ፈጠራ አኳያ፣ የመስሪያ ቦታዎችን ከማዘመን አንጻር፣ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ከመደገፍ አኳያ፣ የኑሮ ውድነትን ከመቀነስ ጋር በተያያዘ እንዲሁም የህብረት ስራ ማህበራትን ከማጠናከር አንጻር የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸዋል።
በአብርሃም አበበ
መጋቢት 25/2016 ዓ.ም