የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደሮች ልማት ተገቢነት ፣አስፈላጊነት እና ትግበራ ላይ የምሁራን ምልከታ በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት ተካሄደ

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 89


የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደሮች ልማት ተገቢነት ፣አስፈላጊነት እና ትግበራ ላይ የምሁራን ምልከታ በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት ተካሄደ

የአዲስ ከተማ አስተዳር በኮሪደሮች ልማት ተገቢነት ፣አስፈላጊነት እና ትግበራ ላይ የምሁራን ምልከታ በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት አካሂዷል፡፡
በፓናሉ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ይህ ከተማችንን የማደስ እንደስሟ አዲስ ፣እንደ ስሟ ውብ ከተማ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ፣በታሰበው ጊዜ ግቡን እንዲመታ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተቀናጀ ርብርብ የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡
በተለይም የዕውቀት ብርሀን የፈነጠቀላችሁ ፣የዓለማችንን ከተሞች እና የህዝቦች አኗኗር የደረሰበትን የዕድገትና የልማት ደረጃ የመመልከት ዕድል የገጠማችሁ ፣ለነገዋ ኢትዮጵያ የተሻለ የምትመኙ በምርጫ ቃል ኪዳናችን መሰረት ፣አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ ፣ነዋሪዎቿ እንድትሆንላቸው በሚፈልጉት ልክ ለኑሮም ለስራም የምትመች ማድረጉ የዚህ ልማት ውጤት ነው ብለዋል፡፤
በፓናሉ የተለያዩ ጽሁፎች ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት በባለ ድርሻ አካላት ተደርጎበታል፡፡
የህ/ግ/ኮ/ዳይሬክቶሬት
መጋቢት 26/2016 ዓ.ም



Leave a Comment: