የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለእርሱ ተጠሪ ከሆኑ ተቋማት መካከል አንዱ ሆነውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን የስራ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 92
ተቋሙ ያለፉት ወራትን የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን በሪፖርቱ መነሻነትም ሰፋ ያሉ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡
መድረኩን የመሩት ክብርት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ተቋሙ በዝግጅት ምዕራፍ ያከናወናቸው ጠንካራ ስራዎች ለተግባር ምዕራፉ ስኬት ጥሩ መደላድል ፈጥረዋል ብለዋል፡፡ በተለይ ከአቻ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት የሄደበት ርቀት ውጤት እንዲያመጣ አስችሎታል ብለዋል፡፡
ለዚህ ለውጥ ደግሞ አይነተኛ ሚና የተጫወተው የስትራቴጂክ ማኔጅመንቱ ያለው ጠንካራ ቅንጅትና በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ተናቦ የመስራቱ ውጤት ነው ብለዋል፡፡ በተለይ የውስጥ አቅምን ከመጠቀም አንጻርም የሰራተኛን ቅሬታ ፈትቶ መሄድ ላይ ፣ምቹ የስራ ቦታና ሁኔታ መፍጠር ላይ ባለሙያው ከአመራሩ ጋር ተናቦ እንዲሄድና በቅርብ ክትትል ለማድግ የተደረገው ጥረት በጣም በጥንካሬ የሚታይና ለሌሎችተቋማትም በተሞክሮነት ሊወሰድ የሚችል ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል፡፤
በቀጣይም ተቋሙ በታዩ ለውጦች ሳይኩራራ ራሱን ከትልልቅ የሚዲያ ተቋማት ጋር የራሱን አቅምና ሁኔታ ባገናዘብ መልኩ በማወዳደር የአዲስ አበባን ለውጥ ቀድሞ ለህዝባችን ብሎም ለአለም በማሳየትና ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ በመሆን በትኩረት ሊሰራ ይገባዋል ብለዋል፡፡
የህ/ግ/የኮ/ዳይሬክቶሬት
መጋቢት 26/2016 ዓ.ም