ሁሉም ዓይነት የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦች ያላት ሀገራችን መስህቦቿን ለማልማት ለማስተዋወቅና በመሸጥ ለኢኮኖሚያችን ዕድገት ዘርፉ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ለማስቻል በትኩረት እየተሠራ ነው። /የተከበሩ አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 23


ሁሉም ዓይነት የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦች ያላት ሀገራችን መስህቦቿን ለማልማት ለማስተዋወቅና በመሸጥ ለኢኮኖሚያችን ዕድገት ዘርፉ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ለማስቻል በትኩረት እየተሠራ ነው። /የተከበሩ አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር

ሁሉም ዓይነት የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦች ያላት ሀገራችን መስህቦቿን ለማልማት ለማስተዋወቅና በመሸጥ ለኢኮኖሚያችን ዕድገት ዘርፉ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ለማስቻል በትኩረት እየተሠራ ነው። /የተከበሩ አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር/ የሲዳማ ሕዝቦች የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በአዲስ አበባ ደረጃ በወዳጅነት አደባባይ በድምቀት ተከብሯል። በበዓል አከባበሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዳስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ሁሉም ዓይነት የተፈጥሮ፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦች ያላት ሀገራችን መስህቦቿን በማልማት በማስተዋወቅና በመሸጥ ለኢኮኖሚያችን ዕድገት ዘርፉ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ለማስቻል በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል። ከአፍሪካ ሀገራት መካከል ግንባር ቀደም ሆና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት በዓለም ቅርስነት ያስመዘገበች ሀገር መሆኗ ደግሞ የዘርፉን የዕድገት ዕድል ያሰፋዋልም ብለዋል። በተለይ ከዘርፉ ዕድሎችና ዕምቅ አቅሞች አንዱ የሆነውን የሲዳማ ሕዝቦች የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ፣ የሁሉም መኖሪያ በሆነችው ከተማችን አዲስ አበባ ዛሬ አክብረናል ያሉ ሲሆን እንዲህ ዓይነት ክብረበዓላት ከተማችንን የሚያደምቁ፤ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ቱሪስቶች እንዲሁም በከተማችን በሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቦች መስህቦቻችንን እንዲያውቋቸው የሚያስችሉ፤ ከተማችንን ተመራጭ የጎብኝት መዳረሻ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል። የህ/ግ ኮ/ዳይሬክቶሬት ሚያዚያ 4/2017 ዓ.ም



Leave a Comment: