በመንግስት ግዥ አፈፃፀም ዙሪያ የሚሰጠው ስልጠና የመንግስት በጀት በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውልና ጤናማ የሆነ የግዥ ስርዓት እንዲፈጠር ትልቅ ሚና እንዳለው ተገለፀ።

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 13


በመንግስት ግዥ አፈፃፀም ዙሪያ የሚሰጠው ስልጠና የመንግስት በጀት በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውልና ጤናማ የሆነ የግዥ ስርዓት እንዲፈጠር ትልቅ ሚና እንዳለው ተገለፀ።

በመንግስት ግዥ አፈፃፀም ዙሪያ የሚሰጠው ስልጠና የመንግስት በጀት በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውልና ጤናማ የሆነ የግዥ ስርዓት እንዲፈጠር ትልቅ ሚና እንዳለው ተገለፀ። በአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ጽ/ቤት የግዥ ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ከተማ ፋይንናስ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት ግዥ አፈፃፀም ስርዓት ዙሪያ ለአመራሩ እና ለጽ/ቤቱ ሠራተኞች ስልጠና ሰጠ። በመድረኩ የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ሐላፊ ወ/ሮ ጀዋሪያ ቀሊ እንዳሉት በመንግስት ግዥ አፈፃፀም ዙሪያ የሚሰጠው ስልጠና የመንግስት በጀት በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውልና ጤናማ የሆነ የግዥ ስርዓት እንዲኖር እንደሚያግዝ ገልፀው ይህም ባለሙያዉ በሂደቱ በቂ እውቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት ኑሮት በቀጣይ እውቀትን መሠረት ያደረገ ግዥ ለመጠየቅም ሆነ ለመፈፀም ያግዛል ብለዋል። የጽ/ቤቱ ሠራተኞችም ስልጠናው የመንግስት ግዥ ሲፈጸም ሀብት እንዳይባክን መመሪያውን ጠብቀን ከኦዲት ነጻ እንድንሆን እና የተቋማችን ሀብትና ንብረት እንዳይባክን ከመጠበቅና ከመከላከል አልፎ ከተጠያቂነት እንድንድን ያስችለናል ብለዋል።



Leave a Comment: