20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአለ አከባበር ላይ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማት፣ ክ/ከተሞች እና አካላት የእውቅና እና የምስጋና ሽልማት ተበረከተላቸው።

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 7


20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአለ አከባበር ላይ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማት፣ ክ/ከተሞች እና አካላት የእውቅና እና የምስጋና ሽልማት ተበረከተላቸው።

20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአለ አከባበር ላይ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማት፣ ክ/ከተሞች እና አካላት የእውቅና እና የምስጋና ሽልማት ተበረከተላቸው። የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመሳተፍ ወደ መዲናችን የመጡ እንግዶችን በክብር በመቀበል፣ በማስተናገድ እና በክብር እስከ መሸኘት በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና የክ/ከተማ ም/ቤቶች ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በበዓሉ ላይ የነበሩ ዋና ዋና ተግባራት ማለትም ከህገ መንግስት አስተህምሮ ጀምሮ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከመፍጠር ፤ ትስስርና አንድነትን ከማጠናከር እንዲሁም ከገበያ ትስስር እና ገጽታ ግንባታ አኳያ አመርቂ ስራ መሰራቱንም የተከበሩ አፈ ጉባኤ ጨምረው ገልፀዋል። በመድረኩ ላይ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ተቋማት እና ክፍለከተሞች የምስጋና የምስክር ወረቀት ከተከበሩ አፈ ጉባኤ እጅ ተቀብለዋል::



Leave a Comment: