ጽ/ቤቱ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ለባለሙያዎቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 6
ጽ/ቤቱ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ለባለሙያዎቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ። በአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመተባበር በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ለአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ፅ/ቤት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል:: መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጀዋሪያ ቀሊ ቴክኖሎጂ በፍጥነት እየሰፋ ሲሄድ መረጃን በደህንነት መጠቀም ከቴክኖሎጂው የበለጠ ትኩረት የሚፈልግ ጉዳይ በመሆኑ በመረጃ አስተዳደርና አጠቃቀም ላይ ልዩ ጥንቃቄ ለማድረግ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ አስፈላጊውን ግንዛቤ መጨበጥ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነም ተናግረዋል። የመረጃ ጥቃት እና የዲጂታል ስርዓቶች መዳከም በተቋማት ላይ ብቻ ሳይሆን በሰፊው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊያመጣ እንደሚችል የገለጹት ኃላፊዋ እንደ ም/ቤት በዲጂታል ቴክኖሎጂ የሰው ኃይል አቅም መገንባትና ማጠናከር ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ በመግለጽ ስልጠናው የመረጃ ጥበቃ ባህልን ለማሳደግ እና የዘመኑን የሳይበር ፈተናዎችን በእውቀት ለመመከት የሚያግዝ ነው ብለዋል። ስልጠናው በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር /INSA/ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ እንደሆነና ዓላማው የሳይበር ምንነት፣ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት፣ የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና መገንባት እና የመረጃ አስተዳደር ደህንነትን ግንዛቤ ማሳደግ እንደሆነ የፅ/ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሀኑ መኮንን አብራርቷል።