የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አመራሮችና አባላት በየተመረጡበት ክፍለ ከተሞች በመገኘት ከነዋሪዎች ጋር የሚወያዩበት የመራጭ ተመራጭ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 7


የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አመራሮችና አባላት በየተመረጡበት ክፍለ ከተሞች በመገኘት ከነዋሪዎች ጋር የሚወያዩበት የመራጭ ተመራጭ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አመራሮችና አባላት በየተመረጡበት ክፍለ ከተሞች በመገኘት ከነዋሪዎች ጋር የሚወያዩበት የመራጭ ተመራጭ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በየካ ክፍለከተማ የተካሄደውን ውይይት የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የመራጭ ተመራጭ መድረኩ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በአመት ሁለት ጊዜ እንደሚካሄድና የአሁኑ መድረክ ደግሞ የበጀት ዓመቱ የማጠቃልያ መድረክ እንደሆነ በመግለጽ ህዝቡ ከዚህ በፊት ሲያነሳቸዉ የነበሩ ጥያቄዎች ከክብርት ከንቲባ እና ከአስፈፃሚ አካላት ጋር በመሆን ምላሽ እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸዋል:: በቀጣይም በከተማችን ዕድገት እስካለ ድረስ ፍላጎቶችና ጥያቄዎች ይጨምራልና አሁንም ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎችን በየደረጃዉ ምላሽ እንዲያገኙ ትኩረት ተሰጠቶ ይሰራልም ብለዋል:: የከተማዉ ነዋሪ ከአሁን ቀደም በተለያዩ መድረኮች ጥያቄ አንስቶ መልስ ያገኙ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች የተሰሩ ተግባራት እና ህዝቡን እና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የተሰሩ የልማት ስራዎችን በክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ቀርቧል።



Leave a Comment: