በጉለሌ ክፍለ ከተማ የመራጭ ተመራጭ ትስስር አደረጃጀት የውይይት መድረክ ተካሂዷል::
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 8
በጉለሌ ክፍለ ከተማ የመራጭ ተመራጭ ትስስር አደረጃጀት የውይይት መድረክ ተካሂዷል:: ውይይቱን የመሩት በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ የተከበሩ ዶ/ር ማሾ ኦላና መድረኩ በሁሉም ክፍለከተሞች ከ5000 በላይ ነዋሪችን በማሳተፍ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው ባለፉት 5 ዓመታት በመራጭ ተመራጭ ትስስር አደረጃጀት የህዝቡን ድምጽ ማድመጥና ችግሮችን ለመፍታት መቻሉን አስታውሰዋል ። በዚህም በተሰሩ የህዝብ ውክልና ስራዎች በርካታ የልማት ፣የዲሞክራሲ እና የመልካም አስተዳደር ውጤታማ ስራዎች መስራታቸውን እና ይህ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው ህዝቡ ከመንግስት ጎን በመሆን ቀን ከሌሊት ድጋፍ ሲያደርግ በመቆየቱ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ምክር ቤቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት እቅዱን ከነዋሪው ጋር ማሳካት መቻሉን አስገንዝበዋል ። የመድረኩ ተሳታፊ የሆኑት ልዩ ልዩ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በበኩላቸው ባለፈት 5 ዓመታት እንደ ከተማ ብሎም በክፍለ ከተማ ደረጃ በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶች መሰራታቸውን በመግለጽ በቱሪዝም፣በወንዝ ዳርቻ ልማት ፣በኮሪደር ልማት፣በልዩ ልዩ የልማት ስራዎች ብሎሞ በስራ እድል ፈጠራ ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል። በክፍለ ከተማው የተወከሉ የፌደራልና የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ባለፉት 5 ዓመታት በተሰሩ የህዝብ ወክልና ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት እና ቀጥተኛ ተሳትፎ የማረጋገጥ ስራዎችመሰራታቸውንጠቁመዋል። በመሆኑም በርካታ ህጎች እንዲወጡ መሰራቱን፣ተከታታይ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች መሰራታቸውን በዚህም በመሰረተልማት ትልቅ እምርታ ያመጣች ከተማ መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል ።