የመራጭና ተመራጭ መድረክ ማህበረሰባዊ ጥያቄዎችን በመመለስ ረገድ ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለጸ።

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 9


የመራጭና ተመራጭ መድረክ ማህበረሰባዊ ጥያቄዎችን በመመለስ ረገድ ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለጸ።

የመራጭና ተመራጭ መድረክ ማህበረሰባዊ ጥያቄዎችን በመመለስ ረገድ ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለጸ። ቦሌ ክፍለ ከተማን በመወከል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ተመራጮች ከመረጣቸው የሕብረተሰብ ክፍል ጋር የውይይት መድረክ አካሂደዋል። በቦሌ ክ/ከተማ የሚካሄዱ የመራጭና ተመራጭ መድረኮች እስከ ዛሬ ድረስ የማህበረሰቡን መሰረታዊ ጥያቄዎች በዝርዝር በመለየትና ምላሽ በመስጠት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሪት ፋኢዛ መሀመድ በውይይት መድረኩ ላይ ተናግረዋል። ያለፉት አምስት አመታት በከተማዋ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ለውጥ የመጣበት "የስኬት ዘመን" እንደነበርም የተናገሩት ም/አፈ ጉባኤዋ ወቅቱ የሥራ ዘመኑ ተጠናቆ ወደ ቀጣዩ ምርጫ የሚሸጋገርበት ዋዜማ ላይ መሆኑ ውይይቱን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል። በመጨረሻም የምክር ቤት አባላቱ በቆይታቸው ለህዝቡ የገቡትን ቃል መፈጸማቸውን ገልጸው በቀጣይም ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ንዲጠናቀቁ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡም ቃል ገብተዋል::



Leave a Comment: