ምክር ቤቱ የልምድ ልውውጥ መድረክ አካሄደ።
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 10
ምክር ቤቱ የልምድ ልውውጥ መድረክ አካሄደ። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር የልምድ ልውውጥ መድረክ አካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ጀዋሪያ ቀሊ ይህ አይነቱ በተቋማት መካከል የሚደረግ የልምድ ልውውጥ ለተቋማት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን በመግለጽ ክፍተቶችን ለይቶ እርምት ለመውሰድም አጋዥ መሆኑን ጠቁመዋል ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ መነቴ ሙንዲኖ በበኩላቸው የልምድ ልውውጡ መድረኩ በርካታ ተሞክሮዎች የተገኙበት መሆኑን ገልጸው፤ ለተደረገላቸው አቀባበል እና ማብራሪያ አመስግነዋል ። በመድረኩ ከአደረጃጀት ፣የተቋም ክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን በሚመለከት፣ የህግ አወጣጥ ሂደት በተመለከተ፣ ከህዝብ ግንኙኝነት ስራዎችን አኳያ እንዲሁም አጠቃላይ የምክር ቤት ጽ/ቤቱ የስራ ክንውኖችን አስመልክቶ ሰፊ ማብራርያ ተሰጥቷል ።