የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሁለተኛ ዙር የመራጭና ተመራጭ መድረክ አፈጻጸምን ገመገመ ።

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 10


የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሁለተኛ ዙር የመራጭና ተመራጭ መድረክ አፈጻጸምን ገመገመ ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሁለተኛ ዙር የመራጭና ተመራጭ መድረክ አፈጻጸምን ገመገመ ። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ዙር የመራጭና ተመራጭ መድረክ አፈጻጸምን የሚገመግም የውይይት መድረክ አካሄደ። የምክር ቤቱ የመንግሥት ዋና ተጠሪ የተከበሩ ዶ/ር ማሾ ኦላና በመክፈቻ ንግግራቸው፤ የመራጭና ተመራጭ መድረኮች የሕዝብን ድምፅ በቀጥታ ለመስማትና ዲሞክራሲያዊ ተጠያቂነትን ለማስፈን ያላቸው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ገልፀው መድረኩ ወቅቱ የምክር ቤቱ የሥራ ዘመን ማብቂያ በመሆኑ፣ በቀረበው ሪፖርት ላይ የጋራ ግንዛቤ መያዝ ለቀጣይ ሥራዎች ወሳኝ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል። አክለውም መድረኩ በዋናነት በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርና የልማት ሥራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። በመድረኩ ላይ የምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ የመራጭ ተመራጭ የትስስር አደረጃጀት አመራሮች፣ የክፍለ ከተማ አፈ-ጉባኤዎችና ምክትል አፈ-ጉባኤዎች የተገኙ ሲሆን በየክፍለ ከተማው የተካሄዱ የመራጭና ተመራጭ መድረኮች በጥልቀት ተገምግመዋል። በግምገማውም በሕዝብና በተመራጮች መካከል ያለው ትስስር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ ተመላክቷል።



Leave a Comment: